CITY COUNCIL OF ADDIS ABABA OFFICE OF THE SPEAKER
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ጽ/ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ጽ/ቤት
ራዕይ በ2020ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ከተሞች ተወዳዳሪና የአፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማዕከል የሚያሰኛት የመሬት ልማት፣ ግብይት፤ የቋሚ ንብረት ዋስትና የተረጋገጠባት፤ በፕላን የምትመራ፤ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ የለወጠች ዘመናዊነት የሚታይባት ከተማ ማድረግ፡፡
የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ማዕከል ዋነኛ ግብ የሀገራችን የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ስርዓት በዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ሙያተኞች በሚፈለገው ብዛት ፣ብቃት እና ጥራት በራሱ የሚተማመን ጠባቂነትን የሚጠየፍ ፣ድህነትን በየደረጃው በመሸራረፍ የሚያፈርስ ፣ስራ ፈጣሪ የህዝቡን ኑሮ ደረጃ በደረጃ ሊቀይር የሚያስችል አቅም ያለው ብቁ የስራ ኃይል መፍጠሩን በስልጠናም ሆነ በልምድ የተገኘውን ዕውቀት ፣ክህሎት እና አመለካከት በተዘጋጀው የሙያ ደረጃ መሰረት ምዘና በማዘጋጀት እና በመመዘን ብቃቱንም በማረጋገጥ ብቁ ዜጋ ለገበያው መመገብ ነው፡፡በዚህ ሂደት ለመመዘን የቀረበ ያንድ ሙያ መስመር ባለቤት በዚህ መስመር በሚገኝበት ደረጃ የሚጠበቅበት ዕውቀት ፣አመለካከት እና ቴክኒካዊ ክህሎት በተቀናጀ አግባብ አሟልቶ ስለማግኘቱ የምዘና መሳሪያ በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት በመጠቀም ዳኝነት በመስጠት ብቁ የሰው ኃይል ለኢንዱስትሪው ለመመገብ ነው፡፡ገና ብቁ ላልሆነ ተመዛኝም ያለበት ክህሎት ክፍተት በዝርዝር ተነግሮት ክፍተቱን በስልጠና እንዲሞላ እና ወደ ብቁነት እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታ ይፈጠርለታል፡፡እንዲሁም ሰርተፊኬት መስጠት እና የእድሳት አገልግሎት መስጠት የመዛኝ፤ ምልመላ ማካሄድ እውቅና መስጠት ፤እድሳት መስጠት የምዘና ጣቢያ ምስረታ እና እውቅና መስጠት ይገኙበታል፡፡ምዘና ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንዲሁም በብቃት አሃድ ለተመዛኞች ይሰጣል፡፡
በሀገራችን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ወደ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ለተሸጋገሩ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ የመንግስትና የግል ልማት ግርጅቶች ውስጥ ላሉት የሰው ኃይል በፍላጎት የተመሰረተ ችግር ፈቺ የሆነ የስልጠና ፡የምርምርና የምክር አገልግሎት በመስጠት የስራ አጥነትን ችግር ለመፍታት የሚያስችልና ውጤታማ የሆነ ልማት የሚያስመዘግብ አቅም መፍጠር ነው፡፡
ክላሲክ የትምህርትና ሥልጠና ኔትዎርክ ኃላ.የተ.የግ.ማህ