Governmental Organizations
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተለያዩ የአገሪቱ ሥነምህዳሮች መሰረት በማድረግ የተቋቋሙ 16
የፌደራል ግብርና ምርምር ማዕከላት የተለያዩ የግብርና ምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን በመጀመሪያው
የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢንስቲትዩቱ 878 ቴክኖሎጂዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ለአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ
ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉና ከውጭ የሚገባ ምርትን ለመተካት የሚያስችሉ የተለያዩ ዝርያዎችን በማቅረብና ባለ
ፋብሪካዎችንና አምራቾችን በማስተሳሰር ለአግሮ ኢንዱስትሪ ልማት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ምርምሩ የዓለም ገበያ የሚፈልገውን ጥራት የሚያሟሉና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ቴክኖሎጂዎችን
በማቅረብ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ ፕሮግራም ለ497,219 ተጠቃሚዎች
አዳዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ፍላጎት መፍጠር የተቻለ ሲሆን በመነሻ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ረገድም ባለፉት
4 ዓመታት ከ 53,830.57 ኩንታል በላይ መነሻ ዘር በማቅረብ ለምርጥ ዘር አቅርቦት ጉልህ አስተዋፅኦ አድርጓል፡