የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ
መድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በተሽከርካሪ ምክንያት እየደረሰ ያለው አደጋ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱና በዚህም ምክንያት የሚደርሰው የሠው ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ኪሳራ ማህበራዊ ችግር የሚያስከትል መሆኑን በማሰብ የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ስርዓት ማመቻቸትና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የተሽከርካሪ አደጋ ሶስተኛ ወገን መድን ሽፋን እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢፌዴሪ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 799/2005ን ለመፈፀምና ለማስፈፀም የተቋቋመ የፌደራል መንግስት ተቋምነው፡፡