Search results for - dessie
-
-
-
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር
የትናንቷ መንቆረር የአሁኗ ደብረ ማርቆስ የተቆረቆረችው ከዛሬ 163 ዓመት በፊት በደጃዝማች ተድላ ጓሉዘመነ መንግስት በ1845 ዓ.ም ነበር፡፡ ንጉስ ተ/ሃይማኖት በ1872 ዓ.ም ጥር ወር ከነገሱ ከሁለት አመት በኋላ በ1874 ዓ.ም የደብረ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ሲተከል ይፋ የሆነው የደብረ ማርቆስ መጠሪያነት በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስት የቀጠለ ሲሆን በተለይ የቀበሌ አስተዳደሮች ባልተቋቋሙበት በጥንቱ ጊዜ ሰፈሮች የየራሳቸው መጠሪያ እንደነበራቸው የከተማዋ የእድሜ ባለፀጋዎች ይናገራሉ፡፡ በዚያን ዘመን የነበረው የከተማዋ ስሪት /አስተዳደር/ ዘውዳዊ ስርዓትን የተከተለ በመሆኑ ለደጃዝማች፣ ለፊታውራሪና ለሌሎችም ሹማምንቶች እና መኳንንቶች ማህበራዊ አገልግሎት የሚያቀርቡ ሰዎች በከተማው ውስጥ የየራሳቸው መንደርና ሰፈር ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ የሰፈር ስያማዎችም በመቅቱ የነበረውን አጠቃላይ ማህበራዊ አገልግሎት መሰረት በማድረግ የተሰጣቸው ነበር፡፡ በንጉሱ ዘመን የጐጃም ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን ያገለገለችው ደብረ ማርቆስ “ካህን ሰፈር” “ፈረስ ቤት” “ቅሬ ሰፈር” ነጋሪት መች ሰፈር” “ሠፊ ሰፈር” “ተልባ ሰፈር” “ደመራ ሰፈር” “ሀይሉ ገበያ/ማክሰኝን ሰፈር” “ግምጃ ቤት” ና “ባሶ በር” አብማና ድብዛ የሚባሉ የመንደር መጠሪያ ስያሜዎች የነበሯት ሲሆን አሁን ከተማዋ በ7 ቀበሌ አስተዳደሮች የተዋቀረች ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በፊት የነበሩ የሰፈር ስያሜዎች ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎችን ስያሜዎች የከተማው ህብረተሰብ በተለይም የአሁኑ ትውልድ ሲጠቀምባቸው አይታይም፡፡
-
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር
የትናንቷ መንቆረር የአሁኗ ደብረ ማርቆስ የተቆረቆረችው ከዛሬ 163 ዓመት በፊት በደጃዝማች ተድላ ጓሉዘመነ መንግስት በ1845 ዓ.ም ነበር፡፡
-
-
-
-
-
-