የደቡብ ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
የደቡብ ቴሙትሥ ቢሮ በክልሉ መንግሥት አዋጅ ቁጥር 133/2003 ተቋቁሞ ሲሠራ ቆይቶ ባሁኑ ወቅት በተሻሻለው አዋጅ ቁ.161/2008 እንደገና ተጠናክሮ የተቋቋመ መንግሥታዊ አካል ነው፡ ሴክተሩ ለዘላቂው የህዳሴ ጉዞ መዳረሻ ሆኖ ለተቀረጽው 2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ዕትዕ) ስኬት ያለውን ቆራጥነት ለማሳየት፣ ‘ህዳሴ ኢትዮጵያ በቴክኒክ ሙያ‘ የሚል መሪ ቃል ይዞ ተነስቷል፡፡