Search results for - mekelle
-
-
-
-
-
ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ደደቢት የብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ ላለፉት 23 ዓመታት በገጠር በእርሻ ስራ ለሚተዳደሩ፣ በከተሞች የጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ለሆኑ፣ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሕብረተሰቡ ክፍሎች ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የህግ ታራሚዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎችና ሌሎችም ዜጎች ገቢ በማሳደግና በመጨመር በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶች በመስጠት ድህነት የማስወገድ ራእይ ይዞ የክልላችን ብሎም የሃገራችን ኢኮኖሚ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲያድግና እንዲቀጣጠል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ቀልጠፋ፣ ስኬታማና ሁሉ ኣቀፍ የፋይናንስ አገልግሎት ለማረጋገጥ ከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ በመጠቀም ደንበኞቹን ከአዳዲስ የንግድ ስራዎች ጋር እንዲተዋወቁ፣ የተሻለ ገበያ እንዲመርጡ፣ የፋብሪካ እቃዎች ከመሸጥና መለወጥ፣ የመጠጥና ምግብ ስራዎች፣ የብረታ ብረትና የእንጨት ስራዎች፣ ከዘመናዊ እርሻ፣ ኮንስትራክኽን ስራዎች፣ ከኢንዱሰትሪ፣ አግሮኢንዱስትሪ፣ ወዘተ ጋር እንዲተዋወቁ በሚያስችል መንገድ ተደራሽነት ፈጥረዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ዜጎች ካላቸው ገቢ በማካፈል የቁጠባ ባህላቸው እንዲያሳድጉ፣ በእቅድ እንዲመሩ፣ የገቢ ምንጭ በማስፋት በራስ የመተማመን ኣቅም እንዲፈጥሩ ለማድረግ በቅርበት በመስራት ላይ ነው፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ተቋሙ የሓዋላ አገልግሎት፣ የቼክ፣ የመድህን ኢንሹራንስ፣ የጡረተኞች ክፍያ፣ የወርቅ ግዢ፣ የመሳሰሉትን አገልግለቶች እየሰጠ ነው፡፡ ቀጣይና የተሟላ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችለን የኮር ባንኪንግ ሲስተምና የኤም. ብር አገልግሎት ኣጠናክሮ እየሄደ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ በሚቀጥሉት አድራሻዎች ሊያገኙን ይችላሉ፡፡
-
-
-
-
-