Search results for - mekelle
-
-
-
-
-
-
-
መቀሌ ከተማ አስተዳደር
ራዕይ vision መቐለ ከተማችን መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ፣ ትምህርትን ማዕከል ያደረገ ድህነት የተወገደባት ዘመናዊ የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ሆና ማየት፣ ተልዕኮ Mission ሁሉንም የልማት ኃይሎች በማቀናጀት እና በማቀሳቀስ ያለንን አቅም ሀብት በአግባቡ በመጠቀም /መጨመር/ የከተማችንን ሥራ አጥን በማስወገድ የ ንግድና ኢንዱስትሪ ማዐከል በማድረግ ልማና መልካም አስተዳደርን ማስፈን:: መቐለ በሰሜናዊ የሀገራችን ክፍል ከአዲስ አበባ በ 778ኪ.ሜ እርቃ ትገኛለች:: በ 13° እና በ21° በሰሜን 29° እና 28° ምስራቅ ትገኛለች:: መቀሌ ከተማ ከ2,000-2,200 ሜትር ከባህር ወለል በላይ የተቀመጠች ስትሆን አመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠን 618 ሚ.ሊ ይሆናል:: የአየር ፀባይዋ ወይናደጋ ሲሆን መካከለኛ 17.6ዲግሪ ሴንቲግሬድ ዝቅተኛ 11° ሴንቲግሬድ እንዲሁም ከፍተኛ 24° ሴንቲግሬድ ስለሆነ ለኑሮ ምቹ ነው ተብሎ ይታሰባል:: ከተማችን 14ኛ ክፍለ ዘመን ሕዝብ መኖር የጀመረባት ስትሆን የነገስታት መቀመጫ የሆነችው ግን በ 19ኛው ክፍለ ዘመን በዘመነ አፄ ዮሐንስ 4ኛ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል እስከ ቅርብ ጊዜ መቀሌ “ምአም አንበሳ” ተብላ ትጠራ ነበር:: መቐለ በዘመነ አፄ ዮሐንስ ለ18 አመታት የሀገራችን ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች:: ከአፄ ዮሐንስ ሞት በሆላ በርከት ያሉ መአከላዊ አስተዳደር አደርገዋት ቆይተዋል:: ከተማችን በተለያዩ የንግድ እንቀስቃሴዎች ረጅም ልምድ እና ታሪክ አላት:: ከቀድሞ ጀምሮ ከምጽዋ ወደ ቃፍ ላይ መተላለፊያ እንደነበረች የተለያዩ ፅሑፎች ያመለክታሉ:: ከዚህ የታሪክ አመጣጥ ጋር የሚመስል የመቀሌ ህዝብን እና የሃውዜን አካባቢ በንግድ ስራዎች ላይ የበለጠ ልምድ እንዳላት ይታወቃል:: ይህ በቻ ሳይሆን የመቐለ ከተማ ከምጽዋ ወደብ 420 ኪ.ሜ ርቀት ሰለምትገኝ ለምስራቅ እና ምእራብ ሃገራት አማካይ ሆና ታገለገል ነበር:: በአሁኑ ሰዓት የመቐለ ከተማ ሕዝብ ከ400,000 በላይ እንደሚሆን ሲገመት፣20.6 ሄክታር የሚያህል የመሬት ስፋት አላት:: ህዝቦችዋም ሰው አክባሪ እና እንግዳ ተቀባዮች ናቸው:: ሰሜናዊቷ ኮከብ ከተማችን ከተለያዩ ጊዜ ትላልቅ ከተሞች ጋራ የሚያገናኛ መንገድ /አስፋልት ስላላት ከዚህም ከዚያም በርካታ ህዝቦች የሚስተናገዱባት ከተማ ናት:: ከተማችን መቐለ ብዙ መሰረታዊ ልማቶች የተስፋፉባት ስትሆን ኢንቨስተሮችም ለኢንቨስትመንት የሚመኟት ከተማ ሆና ትገኛለች:: ከዚህም አልፎ መቐለ ለኢንቨስትመንት የሚያስፈለጉ እንደ አየር ማረፊያ ፣ ባንክ ፣ ኢንሹራንስ ፣ የተማረ የሰው ኃይል ፣የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪ አሸጎዳ፣ ተከዜ ሃድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የተለያዩ የልማት ተቋማት እና የተሻለ ጥሩ አስተዳደር ያላት በመሆኗ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል:: ከተማችን ለኢንቨስትመንት ያላትን መሬት ተጠቅማው በርከት ያሉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ ባለ ሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ሀገራቸውን መጥቀም ላይ ናቸው:: ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከተማችን ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማለትም በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳና በቆዳ ውጤቶች፣ በሆቴል፣ በእንሰሳት ተዋፅኦ ምርቶች፣ በኮንስትራክሽን እቃዎች፣ በበርበሬና የበርበሬ ውጤቶች፣ በአበባ ምርቶች ገና ያልተነኩ የመቐለ ከተማ የኢንቨስትመንት መስኮች ናቸው:: የመቐለ ከተማ ከተጠቀሱትም በላይ ለሌላ አገልግሎት የሚውል ሰፊ መሬት አዘጋጅታ ፍጥነቱን እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቶን አጠናቃ ትገኛለች:: ከተማችን የተለያዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የቱሪስት መስህብ ያላት ስትሆን ሃውልት ሰማዕታት፣ የአፄ ዮሐንስ ቤተ-መንግስት አብረሃ ካስትል ሰላሴ ጨለቆት እና የመስቀል በዓል አከባበር የቱሪስት ከልብን ለመሳብ የቻሉ ናቸው::
-
MEKELE CITY MAYOR OFFICE
መቀሌ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት
-
-