የትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ
P.O.Box 225የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ለአገራዊ እድገት ያለው ፋይዳ የማይተካ መሆኑን በመገንዘብ ለሴክተሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ በጀት እየመደበ ሰፋፊ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ባለፉት ሰባት ዓመታት የአርሶ ኣደሩና የከተማው ህብረተሰብ አስተሳሰብና ጤና በማጎልበት ምርታማነቱን የሚያሳድጉ የተለያዩ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሰጡና ለሁሉም ተደራሽ የሆኑ ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎች በገጠርም ሆነ በከተማ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት በመጀመራችው እናቶች በጤና ተቋሞች የሚወልዱበት፣አርሶ አደሮች እንደ ምርጥ ዘር፣ ማዳበርያና ሌሎች የእርሻ ግብአቶችና ቴክኖሎጂዎች በጊዜና በቀላሉ የሚያገኙበት፣ ያመረቱት ምርት በሃገርና በአለም ገበያ ቀርቦ ተወዳዳሪ በመሆን በተሻለ ዋጋ እንዲሸጥና ኢኮኖሚያዊ ኣቅማቸው በማጎልበት ወደ ኢንዳስትሪ መር ለሚደረገው ሽግግር የራሳቸው ሚና እንዲወጡ እያደረገ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት የተቀዳጀ ኢኮኖሚ፣ በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ብቃት ያለው አንድ ፖለቲካዊ ማህበራዊ በመፍጠር ህብረተሰባችን ደረጃውን የጠበቀ የትራንስፖት አገልግሎት በማግኘት ከቦታ ቦታ የሚነቀሳቀስበት፣ የግልና የወል ፍላጎቱን የሚያሟላበት ሁኔታ ለመፍጠር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት መጥቷል፡፡ በዚህ መሰረት የመንገድ መሰረተ-ልማት ስራዎች ብምናይበት ጊዜ በክልሉ በ1984 ዓ/ም ከነበረው 906 ኪ.ሜ. ደረጃውን ያልጠበቀ መንገድ በአሁኑ ጊዜ በፌደራል መንግስት፣ በመንገድ ስራዎች ኢንተርፕራይዝና በገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም (URRAP) በተሰሩ ስራዎች በአሁኑ ጊዜ የክልሉ የመንገድ ሽፋን 6,452.66 ኪ.ሜ. ደርሷል፡፡ከዚሁ 2,157 ኪ.ሜ. የአስፋልት መንገድ ነው፡፡በዚህ የመንገድ ሽፋን የተሳሰሩ የትግራይ ቀበሌዎች በምናይበት ጊዜ በእቅዱ መጀመርያ በትግራይ ክልል የነበሩ ቀበሌዎች 712 ሲሆኑ ከነዚህ 585 (82.%) ቀበሌዎች ክረምት ከበጋ በሚያገናኝ መንገድ እንዲተሳሰሩ ተደርጓል፡፡የተቀሩት ቀበሌዎችም በሁለተኛው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ጊዜ እንዲተሳሰሩ ትኩረት ተደርጎበት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የመንገድ ተደራሽነት በ2002 ዓ.ም. 56 ኪ.ሜ በ1,000 ሜትር ስኴር የነበረ ሲሆን በ2007 ዓ.ም መጨረሻ 117.4 ኪ.ሜ.በ 1,000 ሜትር ስኴር ደርሷል፡፡በዚህ መሰረት አንድ ሰው ክረምት ከበጋ ወደሚያስኬድ መንገድ ለመድረስ እስከ 2002 ዓ.ም. 6.22 ኪ.ሜ. መጓዝ ይጠበቅበት የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ወደ 2.9 ኪ.ሜ. ቀንሷል፡፡የባቡር መንገድ መሰረተ-ልማትም ከመቐለ-ሃራገበያ-አዋሽ-ጅቡቲ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ ስራዎች በመካሄድ ላይ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገባ የገቢና ወጪ እቃዎች በብዛትና በአነስተኛ ዋጋ በቀላሉ እዲወጡና እንዲገቡ በማድረግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት የላቀ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡አዲስ መስመር የህንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ስራዎች ስንመለከት በዚህ ዋና የስራ ሂደት የተሰሩ ስራዎችን ከ 2003 እስከ 2008 ዓ/ም መጨረሻ ባሉት ጊዜያት በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በህዝብ ተሳትፎ ከ2.8 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 4,571 ማህበራዊና ኢኮኖምያዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ተገንብተው ወደ አገልግሎት ተሸጋግሯል፡፡ከላይ የተጠቀሱት ፕሮጀክቶች ለመገንባት የክልሉ መንግስት የአንበሳው ድርሻ የሚወስድ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ተቋማትም በልማት ስራው የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ድርጅት (EFFORT) ከ120 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችና የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማትን በመገንባት ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ኣድርጓል፡፡ባለፈው 7 ዓመታት ለ294,035 ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡ከነዚህ 46.2% ሴቶች ናቸው፡፡ በትራስፖርት አገልግሎትና የመነሃርያ አስተዳደር የስራ ሂደትም የክልላችን የመንገድ ትራንስፖርት 90 % የህዝብ እንቅስቃሴና 95 %የገቢና ወጪ እቃዎች የሚንቀሳቀሱበት ዘርፍ ነው፡፡በዚህም በክልሉ 270 የትራንስፖርት መስመር የተፈጠረ ሲሆን በ2009 ዓ.ም ብቻ 52,958,946 የሚሆን ህዝብ ከቦታ ቦታ በማጓጓዝ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡እንዲሁም በአሽከርካሪዎች ተሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ የስራ ሂደት ከ2003 ዓ.ም እስከ ጉንበት 2009 ዓ.ም ባሉት አመታት ለ90,480 ተሽከርካሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዓመታዊ ምርመራ የተከናወነ ሲሆን ለ23,071 ተሽከርካሪዎች ብቃታቸውን በማረጋገጥ አዲስ የሰሌዳ ቁጥር በመስጠት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደረጓል፡፡ከዚሁ በተጨማሪ 1,666 ሴቶች የሚገኙበት ለ59,212 ወገኖች የፅሁፍና የተግባር ፈተና በመስጠትና ብቃታቸው በማረጋገጥ አዲስ መንጃ ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ከመጀመርያው የእድገትና የትራንሰፎርሜሽን እቅድ ጀምሮ እስከ አሁን ባለው የአፈፃፅም ሁኔታ ማየት የሚቻለው አፈፃፀሙ ከአመት አመት እያደገና እየጎለበተ የመጣ መሆኑ፤ እቅዶቹን በተደራጀ ልማታዊ ሰራዊት በማስፈፀም ረገድ ዓበይት ለውጦችን እያስመዘገበ እየሄደ ያለ ሴክተር መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በመሆኑም እስካሁን ያስመዘገብናቸው ጥንካሬዎች በመያዝና በማስፋት፣ በአፈፃፀማችን ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ደግሞ በተደራጀ እንቅስቃሴ በማስተካከል ከሰራን በሁለተኛው የእድገትና የትራንፎርሜሽን ዘመን የታቀደውን እቅድ ያለ ጥርጥር ተፈፃሚ እንደሚሆን የሚያመለክት ነው፡፡